የባለአክሲዮኖች 18ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ
Posted on: 05 Nov, 2024
የባለአክሲዮኖች የ18ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የስብሰባ ጥሪ
የተከበራችሁ የማህበሩ ባለአክሲዮኖች
በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ ሕግ አንቀፅ 366፣ 367፣ 370፣ 371፣ እና 372 እንዲሁም በአክሲዮን ማህበሩ የተሻሻለው የመመስረቻ ጽሑፍ አንቀጽ 14.2.1 መሰረት የባለአክሲዮኖች 18ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ቅዳሜ፣ ታህሳስ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ በኢትዮጵያ ሆቴል (ብሔራዊ ትያትር አካባቢ በሚገኘው ቁጥር 1) ስለሚካሂድ የአ/ማኅበሩ ባለአክሲዮኖች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ በስብሰባው ላይ እንድትገኙ የአ/ማኅበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል።
የአክሲዮን ማህበሩ መረጃ
• የአክሲዮን ማህበሩ ስም፡ ዳይናሚክ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ
• የአክሲዮን ማህበሩ የዋና መ/ቤቱ አድራሻ፡ አዲስ አበባ ከተማ፣ ልደታ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 09፣ የቤት ቁጥር አዲስ፣ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ፣
• የአክሲዮን ማኅበሩ ድረ-ገጽ፡ https://www.dynamicmfi.com
• የአክሲዮን ማህበሩ የንግድ ምዝገባ ቁጥሩ፡ LD/AA/2/0008534/2015 ፣
• የአክሲዮን ማህበሩ ዓይነት፡ በአነስተኛ የፋይናንስ ስራ ላይ የተሰማራ፣
• የአክሲዮን ማህበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ ብር 158,913,000፣
• የአክሲዮን ማህበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ ብር 150,122,000፣
የ18ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ረቂቅ አጀንዳዎች
-
የጉባዔውን ረቂቅ አጀንዳዎችን ማፅደቅ፤
-
አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበልና የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን ማሳወቅ፤
-
እ.ኤ.አ. የ2024/2025 ሂሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥና ተወያይቶ ማፅደቅ፤
-
እ.ኤ.አ. የ2024/2025 ሂሳብ ዓመት የውጭ ኦዲተር ሪፖርት ማዳመጥና ተወያይቶ ማፅደቅ፤
-
እ.ኤ.አ. የ2024/2025 ሂሳብ ዓመት የአ/ማኅበሩ ዓመታዊ ትርፍ/ኪሳራ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
-
እ.ኤ.አ. ከ2025/2026 እስከ 2027/2028 ሂሳብ ዓመት ድረስ አክሲዮን ማህበሩን የሚያገለግሉ የውጭ ኦዲተሮችን ሹመት ማፅደቅና የአገልግሎት ክፍያቸውን መወሰን፤
-
እ.ኤ.አ የ2025/2026 ሂሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ክፍያ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤ እና
-
የጉባዔውን ቃለ-ጉባዔ ማፅደቅ።

ማሳሰቢያ
● ባለአክሲዮኖች ለጉባዔው ሲመጡ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው መሆኑን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ/ፓስፖርት ዋናውንና አንድ ኮፒ ይዘው መምጣት ይኖርባቸዋል። በጉባዔው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ጉባዔው ከሚካሄድበት እለት 3 የስራ ቀናት አስቀድሞ ከላይ በተገለፀው የአክሲዮን ማህበር ዋና መስሪያ ቤት አድራሻ በአካል በመገኘት የውክልና ፎርም (ቅፅ) በመፈረም ተወካይ መወከል ይችላሉ።
● በውል አዋዋይ የተረጋገጠና ድምፅ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ማስረጃ ያለው ተወካይ ዋናውን እና አንድ ፎቶ ኮፒ ይዞ በመቅረብ በጉባዔው መሳተፍ ይችላል።
የዳይናሚክ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ.
የዳይሬክተሮች ቦርድ
Comments (0)
Post Your Comment