ከአጭበርባሪዎች ይጠንቀቁ!
May 6, 2026 By Admin User 5 min read
ለዳይናሚክ ማይክሮ ፋይናንስ ደንበኞች በሙሉ ቤተሰብ፣ ወዳጅ፣ ዘመድ ወይም ጓደኛ በመምሰል  በቴሌግራም፣በዋትስአፕ፣ በፌስቡክ ወይም በኢሜል፣ የጽሁፍ መልዕክት ወይም የስልክ ጥሪዎች የሚመጣልዎትን የገንዘብ ማስተላለፍ ጥያቄዎች ከመፈጸምዎ በፊት የጠያቂዉን ማንነት ያረጋግጡ ከማይክሮ ፋይናንሳችን እንደተደወለልዎ በማስመሰል ብድር ሊሰጥዎ ነው እና ገንዘብ ይላኩ የሚሉ እና ሌሎች የረቀቁ የማታለያ ስልቶችን የሚጠቀሙ አጭበርባሪዎች ስለተበራከቱ ለሚደርስዎ ማንኛውም አጠራጣሪ መልእክት በአቅራቢያዎ ወደሚገኙ ቅርንጫፎቻችን በመሄድ ወይም በስልክ ቁጥር 011 515 68 17 በመደወል ሳያረጋግጡ ምንም ዓይነት ውሳኔ እንዳይወስኑ በአክብሮት እናስስባለን፡፡ ዳይናሚክ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ