• info@dynamicmfi.com
  • (+251)115577285

የባለአክሲዮኖች 17ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ

የባለአክሲዮኖች 17ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ

Posted on: 05 Nov, 2024

ዳይናሚክ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. በንግድ ሕግ አንቀፅ 366፣ 367፣ 370፣ 371፣ እና 372 መሰረት ታህሳስ 5 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ ሆቴል መሰብሰብያ አዳራሽ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ የባለአክሲዮኖች 17ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሂዳል። ስለዚህም ባለአክስዮኖች በተጠቀሰው ቀን፥ ሰአትና ቦታ በመገኘት የጉባዔው ተሳታፊ እንድትሆኑ የተቋሙ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል።

1. ስለማህበሩ ዋና ዋና መረጃዎች
1.1     የተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት አድራሻ   አዲስ አበባ፣ልደታ ክ/ከ ወረዳ 09 የቤት ቁ. አዲስ
ድህረ ገጽ፤  www.dynamicmfi.com
1.2     የአክሲዮን ማህበሩ ዓይነት                  አነስተኛ የፋይናንስ ስራ ላይ የተሰማራ የአክሲዮን ማህበር
1.3     የተቋሙ የምዝገባ ቁጥር                    MFI/032/2009
1.4     የተቋሙ የተፈረመ ካፒታል                 ብር 154,421,000
1.5     የተቋሙ የተከፈለ ካፒታል                   ብር 147,172,000
2. የ17ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
1.      የጉባዔውን ረቂቅ አጀንዳዎች ማፅደቅ፣
2.      የአክሲዮን ሽያጭና ዝውውሮችን ማፅደቅና አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበል፣
3.      እ.ኤ.አ. የ2023/24 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ማድመጥና ተወያይቶ ማፅደቅ፣
4.      እ.ኤ.አ. የ2023/24 በጀት ዓመት የኦዲተር ሪፖርት ማድመጥና የአክሲዮን ማኅበሩን የሀብትና ዕዳ ሚዛን እንዲሁም የትርፍና ኪሳራ መግለጫ ላይ ተወያይቶ ማፅደቅ፣
5.      እ.ኤ.አ. የ2023/24 በጀት ዓመት የአክሲዮን ማኅበሩ ዓመታዊ ትርፍ/ኪሳራ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
6.      እ.ኤ.አ. በ2024/25 በጀት ዓመት ተቋሙን የሚያገለግሉ የውጭ ኦዲተሮችን ሹመት ማፅደቅና ክፍያቸውን መወሰን፣
7.      እ.ኤ.አ. የ2024/25 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ክፍያ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
8.      የጠቅላላ ጉባዔውን ቃለ-ጉባዔ ማፅደቅ።

3. ማሳሰብያ

 3.1. በጉባዔው ላይ ለመገኘት የማይችል ባለአክሲዮን ከህዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ልደታ፤ ባልቻ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው ዳይናሚክ ሕንጻ ዋና መስሪያ ቤት የአክስዮን አስተዳደር ቀርበው የውክልና ቅጽ መሙላት ይችላሉ፡፡
 3.2. እንዲሁም በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ የተረጋገጠ በጉባዔ ላይ ለመካፈል እና ድምፅ ለመስጠት ግልፅ ስልጣን የሚሰጥ የውክልና ማስረጃ የያዘ ተወካይ በዕለቱ የውክልናውን ዋና እና ኮፒ እና የባለአክሲዮኑን መታወቂያ ኮፒ ይዞ በመቅረብ በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ይችላል፡፡
 3.3. በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ቀርባችሁ ውክልና የምትሰጡም ሆነ በጉባዔው በአካል የምትገኙ ባለአክሲዮኖች ማንታችሁን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ይዛችሁ እንድትቀርቡ፤ እንዲሁም በውክልና በጉባዔው ላይ የሚገኙ ተወካዮች ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ዋና እና ኮፒ ይዘው መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ባለአክሲዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ቀኑ ያላለፈበት መታወቂያ (ቢጫ ካርድ) ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡


ዳይናሚክ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ

Share This


Comments (0)

No Comment Found!

Post Your Comment