• info@dynamicmfi.com
  • (+251)115577285

የአክሲዮን ሽያጭ ማስታወቅያ

የአክሲዮን ሽያጭ ማስታወቅያ

Posted on: 22 Jul, 2024

የአክሲዮን ሽያጭ ማስታወቅያ
ዳይናሚክ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አክሲዮን ማኅበር በአነስተኛ የፋይናንስ ስራ አዋጅ ቁጥር 626/2009 መሰረት ተቋቁሞ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የስራ ፈቃድ በማግኘት በመስራት ላይ የሚገኝ የፋይናንስ ተቋም ነው። ተቋሙ በ15 ዓመት የአገልግሎት ቆይታው በየጊዜው ሁሉን አቀፍ እድገት በማስመዝገብ ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ የካፒታል አቅሙን ለማጠናከር እንዲረዳው በማቀድ ታህሳስ 6 ቀን 2016 ዓ.ም በተካሄደው 6ኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የተሻሻለው የንግድ ሕግ አንቀፅ 442 በሚፈቅደው መሰረት እያንዳንዳቸው አንድ ሺ ብር ዋጋ ያላቸው 380 ሺ አዲስ አክሲዮኖችን በማውጣት የአክሲዮን ማኅበሩ ካፒታል አሁን ካለበት ከ ብር 120 ሚሊዮን (አንድ መቶ ሀያ ሚሊዮን) ወደ ብር 500,000,000.00 (አምስት መቶ ሚሊዮን ብር) እንዲያድግ ተወስኗል። 


በመሆኑም በቀረበው የባለቤትነት ጥሪ እድል መሰረት፤
  1. ለሸያጭ የቀረበው አዲስ የአክሲዮን ብዛት እንያንዳዳቸው 1,000 ብር ዋጋ ያላቸው 380,000 አዲስ አክሲዮኖች ናቸዉ።
  2. የአንድ አክሲዮን ዋጋ ብር 1,000 (አንድ ሺ ብር) ሲሆን፤ አንድ አዲስ ባለአክሲዮን ሊገዛ የሚችለው ዝቅተኛው የአክሲዮን ብዛት 50 (ሃምሳ) ወይም ብር 50,000 (ሃምሳ ሺ ብር) ዋጋ ያላቸው አክሲዮኖችን ነው፡፡
  3. እስከ 6ኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ድረስ ያሉት ነባር ባለአክሲዮኖች ከፕሪሚየም ክፍያ ነፃ መግዛት የሚችሉ ሲሆን አዲስ ባለአክሲዮኖች ግን በአጠቃላይ በማንኛውም ጊዜ ፈርመው በሚገዙት አክሲዮን ላይ የሚታሰብ 5% (አምስት በመቶ) የፕሪሚየም ክፍያ መክፈል ይጠበቅባቸዋል።
  4. የአክሲዮን የክፍያ ሁኔታ፤

4.1. ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሆነ አክሲዮን ገዢ የአክሲዮንና የፕሪሚያም ክፍያ የሚፈፅመው በኢትዮጵያ ብር ነው።

4.2. ማንኛውም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆነ የውጪ አገር ዜጋ የአክሲዮንና የፕሪሚያም ክፍያ የሚፈፅመው የብሔራዊ ባንክ መመሪያ በሚፈቅደው መሰረት በውጪ አገር ገንዘብ ይሆናል።

4.3. ነባርም ሆኑ አዲስ ባለአክሲዮኖች የፈረሟቸውን አክሲዮኖች: ቢያንስ ግማሹን (50%) ክፍያ የአክሲዮን ግዢ በፈረሙበት ቀን፣ ቀሪ አንድ አራተኛውን (25%) ክፍያ የአክሲዮን ግዢ በተፈረመ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ፣ እንዲሁም የመጨረሻውን ቀሪ አንድ አራተኛ (25%) ክፍያ የአክሲዮን ግዢ በተፈረመ በአንድ ዓመት ጊዜ ወይም ከዚያ በፊት ከፍለው ማጠናቀቅ ይኖርባቸዋል።

5. ማንኛውም ሰው ለመጀመሪያ ዙር አክሲዮን ለመግዛት ሲመጣ የሚከተሉትን ሰነዶች ማቅረብ ይጠበቅበታል፦

5.1. አክሲዮን የሚገዛው ድርጅት ከሆነ ሕጋዊነቱን የሚያሳይ የንግድ ምዝገባ፣ ለዘመኑ የታደሰ የስራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የመመስረቻ ጽሑፍ፣ የድርጅቱን ሕጋዊ ተወካይ የሚያሳይ ደብዳቤ፣ የተወካይ የታደሰ መታወቂያ/ፓስፖርት/መንጃ ፈቃድ ማቅረብ አለበት።

5.2. አክሲዮን የሚገዛው ግለሰብ ከሆነ ማንነቱን የሚያሳይ በወቅቱ የታደሰ መታወቂያ/ፓስፖርት/መንጃ ፈቃድ፣ ተወካይ ከሆነ ደግሞ ከሚመለከተው የመንግስት መ/ቤት የተሰጠ የውክልና ሰነድ ማቅረብ አለበት።

5.3. አክሲዮን የሚገዛው ትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጪ ሀገር ዜጋ ከሆነ ቢያንስ ለ6 ወር የሚያገለግል ፓስፖርትና የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ማቅረብ ይኖርበታል።

6. የአክሲዮን ሽያጭ ከፍያ የሚፈፀመው ለዚህ ተግባር ብቻ በተቋሙ ስም በተከፈቱ የባንክ ሂሳቦች ሲሆን ወደ ባንክ ገቢ የተደረበትን የባንክ ሰነድ (ስሊፕ) ይዞ የአክሲዮኖች ሽያጭ በሚከናወንባቸው ቦታዎች ድረስ በአካል በመቅረብ ወይንም ሕጋዊ ተወካይ በመላክ መግዛት ይቻላል። 


ተ.ቁ
የባንክ ስም
ሒሳቡ የተከፈተበት ቅርንጫፍ
የሂሳብ ቁጥር 
1የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ልደታ ማርያም
1000598380857
2አቢሲኒያ ባንክ  
ልደታ
9999857
3አዋሽ ባንክ 
ጨፌ ሙዳ
13231268072400
4ፀሐይ ባንክ
ልደታ
1003818612
5ቡና ባንክ
ልደታ
1469501007192
6አባይ ባንክ 
ልደታ
1141111023549220
7የኦሮሚያ ኅብረት ስራ ባንክ 
አባ ነፍሶ 
1011100244662
8አማራ ባንክ
ልደታ
9900027715455

ለተጨማሪ መረጃ ዳይናሚክ ሕንጻ (ልደታ፤ ባልቻ ሆስፒታል አካባቢ ፀሐይ ባንክ የሚገኝበት) በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት የአክስዮን አስተዳደር፤ ወይም በስልክ ቁጥር +251115579632 በመደወል አስፈላጊዉን ተጨማሪ ማብራርያ ማግኘት ይቻላል።

“ ይህ ማስታወቅያ እንዲተላለፍ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ተፈቅዷል”

ዳይናሚክ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አ.ማ. 15 ዓመታትን በስኬት!

Share This


Comments (2)

1. Henok Abera

17 Oct, 2024

Dynamic microfinance institution for this initiative to sell additional shares, as it reflects both growth potential ans a commitment to expanding. this srategic move can stregthen the institution's capital base, enabling further financial inclusion and support for small scale enterprises! Well Done!

2. Million Getie

18 Oct, 2024

ዳይናሚክ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አክስዮን ማህበር

በቀድሞ ስሙ ዳይናሚክ አነስተኛ ብድር አቅራቢ ተቋም
ከዛሬ 7 አመታት በፊት ከነበረበት ትልቅ ቀውስ ውስጥ ወጥቶ ዛሬ የራሱ ህንፃ ገዝቶ የህንፃ ባለቤት ሁኗል።
ትልልቅ ተቋማት ጋር የስራ ግንኙነት ፈጥሯል
እንደ
አዋሽ ባንክ
አቢሲኒያ ባንክ
ቡና ባንክ
ፀሀይ ባንክ
ፀሀይ ኢንሹራንስ
ዘመን ኢንሹራንስ
.
.
.

በጣም ብዙ
ከ6 ቅርንጫፍ 29 ቅርንጫፍ ደርሷል ምክንያቱን ከጠየቃችህ

"በዕውቀቱ" ነው
በዕውቀቱ ሰርቶ የሚያሰራ ጀግና የስራ ኋላፊ ብቻ ሳይሆን አባት ነው። ለዚህ እኛ ልጆቹ ምስክር ነን።


@በዕውቀት"
እናመሰግናለን !!!


Post Your Comment