• info@dynamicmfi.com
  • (+251)115577285

ዳይናሚክ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ.ዛሬ እሁድ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም. በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 በተደረገው የልዩ እድር ዓመታዊ ስብሰባ ላይ በመገኘት አላማውንና አገልግሎቶቹን አስተዋወቀ::

ዳይናሚክ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ.ዛሬ እሁድ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም. በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 በተደረገው የልዩ እድር ዓመታዊ ስብሰባ ላይ በመገኘት አላማውንና አገልግሎቶቹን አስተዋወቀ::

Posted on: 21 Oct, 2024

ዳይናሚክ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ.ዛሬ እሁድ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም. በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 በተደረገው የልዩ እድር ዓመታዊ ስብሰባ ላይ በመገኘት አላማውንና አገልግሎቶቹን አስተዋወቀ::

በፕሮግራሙ ላይ የማርኬቲንግና ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ከቃሊቲ ቅርንጫፍ ሰራተኞች ጋር በመሆን የተገኙ ሲሆን የዳይናሚክ አመሰራረትና ከምስረታው ጀምሮ ያከናወናቸውን ስራዎች በጥቅሉ ለአባላት ተገልፆላቸዋል::

በዝግጅቱ ወቅት የዳይናሚክ ማይክሮፋይናንስ የብድርና የቁጠባ አገልግሎቶች የተዋወቁ ሲሆን በእድሩ አባላት በኩልም አገልግሎቶቹን ለመጠቀም ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለ ለመረዳት ተችሏል::

በመጨረሻም በእድሩ አመራር በኩል አባላቶቻቸው እንዲሁም ተመሳሳይ ተቋማትን ከዳይናሚክ  ማይክሮፋይናንስ ተቋም ጋር በጋራ የሚሰሩበት መንገድ ለማመቻቸት የሚችሉትን ሁሉ ጥረት እንደሚያደርጉና ለተደረገላቸው ድጋፍም ከፍተኛ ምስጋናና አክብሮት እንዳላቸው በመግለጽ በግዜ ገደብ ቁጠባ የተጀመረ ግንኙነታቸውንም በሌሎች አገልግሎቶችም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል::

Share This

Comments (0)

No Comment Found!

Post Your Comment