ለዳይናሚክ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ...
የዳይናሚክ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ የባለ አክሲዮኖች 6ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ታህሳስ 6 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የማህበሩ ካፒታል ከ120 ሚሊዮን ብር ወደ 500 ሚሊዮን ብር እንዲያድግና እንደሚከተለው እንዲፈፀም ተወስኗል።
የአክሲዮን ሽያጭ ማስታወቅያ
ዳይናሚክ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አክሲዮን ማኅበር በአነስተኛ የፋይናንስ ስራ አዋጅ ቁጥር 626/2009 መሰረት ተቋቁሞ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ
ባንክ የስራ ፈቃድ በማግኘት በመስራት ላይ የሚገኝ የፋይናንስ ተቋም ነው። ተቋሙ በ15 ዓመት የአገልግሎት ቆይታው በየጊዜው ሁሉን አቀፍ እድገት
በማስመዝገብ ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ የካፒታል አቅሙን ለማጠናከር እንዲረዳው በማቀድ ታህሳስ 6 ቀን 2016 ዓ.ም በተካሄደው 6ኛው አስቸኳይ
ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የተሻሻለው የንግድ ሕግ አንቀፅ 442 በሚፈቅደው መሰረት እያንዳንዳቸው አንድ ሺ ብር ዋጋ ያላቸው 380 ሺ አዲስ አክሲዮኖችን
በማውጣት የአክሲዮን ማኅበሩ ካፒታል አሁን ካለበት ከ ብር 120 ሚሊዮን (አንድ መቶ ሀያ ሚሊዮን) ወደ ብር 500,000,000.00 (አምስት
መቶ ሚሊዮን ብር) እንዲያድግ ተወስኗል።
Aqua for All WASH Finance Ethiopia Project Matching Grant Agreement, between DMFI and Fair and Sustainable Consulting
Aqua for All WASH Finance Ethiopia Project Matching Grant Agreement, between DMFI and Fair and Sustainable Consulting
የባለአክሲዮኖች 17ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ
ዳይናሚክ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. በንግድ ሕግ አንቀፅ 366፣ 367፣ 370፣ 371፣ እና 372 መሰረት ታህሳስ 5 ቀን 2017 ዓ.ም.
በአዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ ሆቴል መሰብሰብያ አዳራሽ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ የባለአክሲዮኖች 17ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሂዳል።
ስለዚህም ባለአክስዮኖች በተጠቀሰው ቀን፥ ሰአትና ቦታ በመገኘት የጉባዔው ተሳታፊ እንድትሆኑ የተቋሙ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት
ጥሪውን ያስተላልፋል።
ዳይናሚክ ማይክሮ ፋይናንስ እና ካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስ በዲጂታል ቁጠባና ብድር አገልግሎት አብሮ መስራት ጀመሩ
ዳይናሚክ ማይክሮ ፋይናንስ እና ካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስ በዲጂታል ቁጠባና ብድር አገልግሎት አብሮ መስራት ጀመሩ::